የኢትዮጵያ ሴቶች ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ተጋጣሚውን አውቋል

በመጪው 2018 ዓ.ም ጥቅምት ወር ላይ በሞሮኮ አስተናጋጅነት ለሚደረገው የሴቶች ከ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ የአፍሪካ ዞን ማጣሪያ ድልድል ይፋ ሆኗል።

በድልድሉ በቋት ሁለት የተመደበው የኢትዮጵያ ሴቶች ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በመጀመሪያው ዙር የማጣሪያ ጨዋታ ከዚምባቡዌ አቻው ጋር ተደልድሏል።

በዚምባብዌ የሚደረገው የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ቀዳሚ ጨዋታ ከጥር 2 እስከ ጥር 5 ባሉት ቀናት መካከል ሲደረግ በኢትዮጵያ የሚደረገው የመልስ ጨዋታ ደግሞ ከሳምንት በኋላ ከጥር 9 እስከ ጥር 12 ባሉት ቀናቶች መካከል ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ የሴቶች ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የዚምባቡዌ አቻውን በደርሶ መልስ ማሸነፍ ከቻለ በሁለተኛው ዙር ማጣሪያ ከግብፅ እና ካሜሩን አሸናፊ ጋር ይጫወታል።