የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
- በየሁለት ዓመቱ ሲካሄድ የቆየው የአፍሪካ ዋንጫ ከ2028 ጀምሮ በአራት ዓመት አንድ ጊዜ እንዲካሄድ ውሳኔ ተላልፏል። በዚህም መሠረት የ2029 የአፍሪካ ዋንጫ ለማሰናዳት ጥያቄ ያቀረበችው ሀገራችን ኢትዮጵያ በ2028 የአፍሪካ ዋንጫ የማዘጋጀት ጥያቄ ውስጥ የሚታይ ይሆናል።
- የሀገር ውስጥ ሊጎች በሚጫወቱ ተጫዋቾች በሚዋቀሩ ቡድኖች መካከል ሲካሄድ የነበረው የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) እንዲሰረዝ ውሳኔ ተላልፏል።
- የአፍሪካ ሀገራት ሊግ (ኔሽንስ ሊግ) ከ2029 ጀምሮ በመስከረም፣ ጥቅምት እና ኅዳር ወራት በየክፍለ አህጉሩ ተከፋፍሎ መካሄድ ይጀምራል።
