የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ 8ኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ተጠባቂ ጨዋታ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም መቻልና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታ ያለ ግብ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት ከተጠናቀቀ በኋላ ሁለቱም አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
የመቻል ዋና አሰልጣኝ ኢንስትራክተር መሰረት ማኔ በጨዋታው ልጆቼ የሰጠሁትን ታክቲክ ተግብሮልኛል ስትል ተናግራለች እኛ አሁንም ቢሆን ከዋንጫ ፉክክር አልወጣንም እስከመጨረሻው ድረስ እንፎካከራለን ሲትል ተናግራለች ።
ጥሩ ጨዋታ ነው ያደረግነው ጥሩ ፉክክር አሳይተናል ያገኘናቸውን ዕድል ብንጠቀም ከዚህ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንችል ነበር ስትልም በአንድ ነጥብ አለመከፋቷን ገልፃለች።
አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና አሰልጣኝ በሰጡት አስተያየት ጥሩ ጨዋታ ነው ያደረግነው ጥሩ ፉክክር ነው ያሳየነው ዛሬ የጣልነው ሁለት ነጥብ ይቆጨናል ብዬ አላስብም በርካታ ጨዋታዎች ከፊታችን ይጠብቁናል በማለት ተናግሯል።
አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ስለ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ግስጋሴ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ኢትዮ ኤሊክትሪክ ተጠናክሮ መምጣቱ ለሊጉ ጥንካሬ ይጨምራል ለሊጉ ሌላ ውበት የጨመረ ቡድን ነው በማለት ተናግሯል።
እኛ ግን ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች ነን ስድስት ጊዜ ዋንጫ ማሸነፍ ችለናል በተከታታይ ዘንድሮም ለሰባተኛ ጊዜ ለማሸነፍ እየሰራን ነው በዛሬ ጨዋታ ክለቡ ያለመሸነፍ ጉዞ በማስቀጠሉ ደስተኛ ነኝ በማለት ሀሳቡን ሰጥቷል።
