የአንድ ሚሊዮን ብር የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት
አሜን አጠቃላይ ሆስፒታል ከየኛ አዲስ ከቴ እግር ኳስ ክለብ ጋር አዲስ አጋርነት ስምምነት ፈፅመዋል።



የኛ አዲስ ከቴ እግር ኳስ ክለብ አመራሮች በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት እንዲህ ያሉ ትብብሮች ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ዕድገት እና ለክለቦች አቅም መጎልበት ወሳኝ ናቸው ያሉ ሲሆን ” በሜዳ ላይ የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ ሌሎችም የስፖንሰር ሺፕ አቅርቦት ስርዓት መዘርጋት አለብን፤ ይህ ስምምነትም የዚሁ አካል ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
የአሜን አጠቃላይ ሆስፒታል ድርጅቱ በበኩሉ፣ በኢትዮጵያ ትልቅ የገበያ ማዕከል ከሆነው መርኬዎቹ እንድሁም በርካታ ደጋፊ ባለቤት ከሆነው የኛ አዲስ ከቴ እግር ኳስ ክለብ ጋር መስራት ለተጠቃሚዎች ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥርለት ገልጿል።
ይህ አዲስ ጥምረት በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን ግንኙነት ከማጠናከሩ ባለፈ፣ ሌሎቹም በአካባቢው ያሉ ባለሃብቶችና ድርጅቶች መሰል ትብብሮች እንዲያደርጉ የሚያበረታታ እርምጃ ሆኖ ተመዝግቧል።
