የቀድሞ ተጨዋች በቤንሻንጉል ጉሙዝ ሊግ ዱል አዘሃቢ እግር ኳስ ክለብ እያሰለጠነ ይገኛል!

► አሰልጣኝ ማንያዘዋል ጎዳዬ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ሊግ ( ቤጉ ሊጉ) ክለብ  ውሉን አራዘመ።

►በባለሀብቱ በአቶ አዎድ የሱፍ  ባለቤትነት የሚመራው እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ (ቤጉ) ሊግ ለሚወዳደረው እና በ2017 ዓ/ም በኢትዮጵያ ክለቦች ሻምፒዮና ተሳታፊ አድርጎት ለነበረው ክለቡ ለዱል አዛሃቢ ለሁለተኛ የውድድር ዓመት ለመቆየት  ፊርማውን አኑሯል።

►ማንያዘዋል ጎዳዬ ከዚህ ቀደም በደቡብ ፖሊስ ፣ መከላከያ (መቻል) ፣ ነቀምቴ ከተማ ፣ ሻሸመኔ ከተማ ፣ ጌዲኦ ዲላ (ይርጋጨፌ ቡና) እና ለቤንች ማጂ  ቡና ተጫውቶ ያሳለፈ  ሲሆን  በአሰልጣኝነትም ሀዲያ ዞንን እና ሆሳዕና ከተማን ለመምራት ችሎ ነበር።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *