ኢትዮጵያ ብቁ እና ጠንካራ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን እንዲኖራት ለማድረግ ዘመኑ የደረሰበትንና አሁናዊ ነባራዊ ሁኔታን ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ስልጠና መስጠት ጨምሮ የሀገሪቱን እግር ኳስ ለማሳደግ ታዳጊዎችን ማብቃት ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ይታወቃል::
ከእነኝህ ስራዎች መካከል በተለያዩ ክልሎች እና ከተማ አሰተዳደሮች ፓይለት ፕሮጀክቱን ለእግር ኳሱ እድገት እየሰራ እንደሆነ ይታወቃል የተቋቋሙት ፓይለት ፕሮጀክቶች ተጠቃሽ ናቸው::
በ2014 ዓ.ም በወላይታ ዞን በወላይታ ሶዶ ከተማም ይህ ፓይለት ፕሮጀክት ተመስርቶ ስልጠናውን የጀመረ ሲሆን ለከተማ ለዞን ለክልልና ለተለያዩ ለኢትዮጲያ ክለቦችን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በርካታ ታዳጊዎችን እያበቃ በሚገኝ የካበተ የአሰልጣኝነት ልምድ ባለቤቱ አሰልጣኝ አንዴቦ ኡሊሶ ይሄንን ኃላፊነት በመውሰድ ላለፉት አመታት ሲተጋ ቆይቷል::
ለአብነትም በ2015 ዓም በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት በሲዳማ ክልል በተደረገው ከ16 በታች ፓይለት ፕሮጀክቶች ምዘና ውድድር አንደኛ ወጥቶ ዋንጫ ከመሳም ባለፈ የጨዋታ ዲሲፕሊን ዋንጫ ክብር ተቀዳጅተዋል::
የወላይታ ሶዶ ፓይሌት ፕሮጀክቱ በዚህ ውድድር የነገይቱ ኢትዮጵያ እግር ኳስ እድገት ተስፋ የሚጣልባቸው ታዳጊዎችን ከማሳየቱ ባለፈ በውጤታማው አሰልጣኝነት አንዴቦ ተደጋጋሚ ዋንጫዎችን ማግኘት የቻለው አሰልጣኝ አንዴቦ ኡሊሶ የብሔራዊ ቡድን ኃላፊነት ቢሰጠውም በብቃት እንደሚወጣው ፍንጭ ያሳየ ነበር::
በዚህ አንድ ያለው የወላይታ ሶዶ ፓይሌት ፕሮጀክት ቡድኑ ጥንካሬ በ2016 ዓም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በሐዋሳ ከተማ ባዘጋጀው የፓይሌት ፕሮጀክቶች ምዘና ውድድር ተሳትፎ ላይ ተፈትሿል:: በጥንካሬ ከተወዳደሩ ቡድኖች ጋር ተፎካክረው ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ የውጤታማነት ምዕራፍ ሁለት ብለው ቀጠለ::
በዚያው አመት የወላይታ ሶዶ ከተማ ስፖርት ምክር ቤት ባዘጋጀው ውድድርም የጠንካራ ስራቸው ውጤቱ ፈርቀዳጅ አድርጏቸው በአንደኛነት ጨርሰውታል:: ውጤታማው አሰልጣኝ አንዴቦ ኡሊሶም የውድድሩ ኮከብ አሰልጣኝ ሆኖ ተመርጧል::
በጥንካሬ የስኬት ማማ ላይ መውጣት የጀመረው የወላይታ ሶዶ ፓይሌት ፕሮጀክት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አዘጋጅነት በተሰናዳው ከ17 ዓመት እድሜ እርከን ተሳትፎ የአንደኝነት ስፍራውን ሳያስደፍሩ የውድድሩ አሸናፊ ሆነዋል::
የኢትዮጵያ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በወላይታ ሶዶ ከተማ ያዘጋጀው የመላው ኢትዮጵያ ውድድርም ለወላይታ ሶዶው ፓይሌት ፕሮጀክት አቅሙን ማሳያ ሆኖት አልፏል:: ከ17 ዓመት በታች ውድድር ላይም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን በመወከል የውድድሩ ምርጥ አሰልጣኝ ተብሎ የተሸለመውን አሰልጣኝ አንዴቦ ኡሊሶንና ምርጥ ስብስብ የያዘው ቡድኑ የአዘጋጅነት ዋንጫውን በክልሉ በማስቀረት እንደተለመደው የውድድሩ አሸናፊ ሆነው የዋንጫ ካዝናቸውን አስፍተውታል::
አሸናፊነታቸው በዚህ አላበቃም:: የኢትዮጵያ እግኳስ ፌዴሬሽን በአዲስ አበባ ባዘጋጀው ከ18 ዓመት በታች የፓይሌት ፕሮጀክቶች ምዘና ውድድር ከለመዱት አንደኝነት ጋር አገናኝቷቸዋል:: በዚህም የውድድሩ አሸናፊነት ዋንጫ ኮከብ አሰልጣኝነት : የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች : ኮከብ በረኛና የውድድሩ ዲሲፕሊን ዋንጫ በአጠቃላይ አምስት ዋንጫዎችን ጠቅልሎ የገባ ቡድን ሆኖ አድናቆት ተችሮታል::
ይህ ማለት የወላይታ ሶዶ ፓይሌት ፕሮጀክት በአንድ አመት ውስጥ የአራት ዋንጫዎች ባለቤት እንዲሆኑ ያስቻለ ሲሆን እንደ አሰልጣኝ አንዴቦ ኡሊሶ አይነቶች ወጣት አሰልጣኞች እድል ቢሰጥ ለእግርኳሳችን ማንሰራራት መፍትሄ ያስገኛል የሚል ድምዳሜ እንዲሰጥ ይገፋፋል ማለት ነው::
ይሄንን የተመለከቱት የወላይታ ዞን አስተዳደርና የወላይታ ሶዶ ከተማ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ቡድኑ ወደ ዞኑ ሲመለስ ደማቅ አቀባበል በማድረግ የእራት ግብዣ አድርገው አመስግነዋል:: ይህ ብቻ ሳይሆን የመጣውን ውጤት አጠናክረው እንዲያስቀጥሉትም ከተማውና ዞኑ በጋራ የ300,000 ሺ ብር ማበረታቻ ሽልማትም አበርክተዋል::
