ዋና አሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊትን ያሰናበተው መቐለ 70 እንደርታ እግር ኳስ አዲስ አሰልጣኝ ሾመ!

በሲቢኢ የኢዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው መቐለ 70 እንደርታ ዋና አሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊትን በማሰናበት ፀጋዬ ኪ/ማሪያምን በድጋሚ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል።

በውድድር ዓመቱ አሥር ጨዋታዎችን አድርጎ አራት ነጥቦች ብቻ በመሰበብሰብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው መቐለ 70 እንደርታ በውጤት ቀውስ ምክንያት ዋና አሰልጣኙን ጌታቸው ዳዊትን በማሰናበት ፀጋዬ ኪ/ማሪያምን ቀጥሯል።