አርባ ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ቦርድ የተለያዩ ውሳኔዎች አስተላለፈ

የአርባ ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ቦርድ ክለቡን ወደ ቀድሞ ውጤታማነቱ ለመመለስ ጠንካራ ውሳኔዎች አስተላለፈ

የቡድኑ ውጤት ማጣት የብቃት፣የዲስፕሊንና የቅንጅት ጉድለት መሆኑን የገመገመው ቦርዱ የአሰልጣኝ ቡድኑን ሙሉ በሙሉ እንዲቀየር ውሳኔ ሰጥቷል።

የአርባ ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ቦርድ በ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ 10ኛ ሳምንት መርሃግብርን በማከናወን በዝቅተኛ ውጤት በሊጉ በመጨረሻ ደረጃ ሰንጠረዥ ላይ የሚገኘው ክለቡን ወደ ቀድሞ ውጤታማነቱ ለመመለስ በአስቸኳይ ስብባው የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፋል።

ቦርዱ እግርኳስ የመደበኛ የኑሮ አካል አድርጎ ለሚወደውና ለሚደግፈው አልፎም ለዘርፉ በርካታ ልጆቹን እያፈራ ለሚገኘው የስፖርቱ ቤተሰብና ስፖርት ወዳዱ ማህበረሰብ በድል የታጀበ ውጤትን ለማምጣት አበክሮ እንደሚሰራም ገልጿል።

በ10 የሊግና የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች የአሰልጣኝ ቡድን ቅንጅት አለመኖር፣ የተጫዋች የአካል ብቃትና የዲስፕሊን ክትትል ጉድለት፣የቴክኒክ ጉዳዮችን በአግባቡ አለመምራትና ውጤትን ለማሻሻል የቡድኑ ትጋት ማነስና የጋራ ኃላፊነት አለመውሰድ በቡድኑ ውጤት ላይ ተፅዕኖ ማሳደራቸውን አፅንኦት በመስጠት ገምግሟል።

ቡድኑ ሕዝባዊ መሠረት እንዲይዝና ደጋፊውና ቦርዱ በስፖርቱ ፍቅር ዋጋ እየከፈለና የሚገባውን እንዲሰጠው በዘላቂነት ውጤት ለማምጣት ከቦርድ ጀምሮ ባሉ የክለቡ አደረጃጀቶ የሪፎርም ሥራዎችን መስራት የተጀመረው መሆኑ የተገለፀ በዛሬው ዕለት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ 15 አባላት የያዘ አዲስ የቦርድ አባላትንና አዲስ ምክትል ሰባሰቢ ያካተተ የአሰልጣኝ ቡድን፣የቴክኒክ ቡድንና የደጋፊዎች ማህበርን የሳይንሱን እና ሙያዊ እውቀት፣ክህሎትና ብቁ ልምድና የሀብት ምንጭ የሚሆኑና ለዘርፉና ለቡድኑ ልዩ ፍቅር ባላቸው ሙያተኞች፣ ተቋማት፣ ድርጅቶችና አባላት በአዲስ መልክ እንዲደራጅ በውሳኔው ገልጿል።

በአዲስ አባላት የሚጠናከረው የክለቡ ቦርድና በአዳዲስ አባላት የሚደራጀው የአስልጣኝ ቡድን፣የቴክኒክ ቡድንና የደጋፊ ማህበር የክለቡ የቀድሞ ክብር ለመመለስ እምነት የተጣለባቸው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ቡድኑ በሜዳ ሆነ ከሜዳ ውጭ ውጤታማ እንዲሆን የግል አበርክቶን ጨምሮ ከፍተኛ የጋራ ሥራ ኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባም ጠቅሷል።

ክለቡን በጊዜያዊነት የሚመሩ የአስልጣኝ ቡድን እጩዎች ላይ እየመከረ የሚገኘው ቦርዱ በከሰዓት መርሃ ግብር ውይይቱን ቀጥሎ እንደሚያካሂድ የተገለፀ ሲሆን የክለቡን ጊዜያዊ የአሰልጣኝ፣የቴክኒክ ቡድንና አዳዲስ የቦርድ አባላትን ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

አርባ ምንጭ ከተማ መ/ኮሚዩኒኬሽን