አርባ ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ቦርድ አበባው ቡታቆን ጊዜያዊ አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ!

የአርባ ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ቦርድ አንጋፋውን የቀድሞ ተጫዋች አበባው ቡጣቆን ጊዜያዊ አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል።

የክለቡን የቀድሞ ውጤታማነትና በሊጉ ያለውን የተፎካካሪነት ጥንካሬውን ለመመለስ የተለያዩ የሪፎርም ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

የአርባ ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ቦርድ የ2018 የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ውድድርን እያካሄደ የሚገኘውና የኢትዮጵያ ዋንጫ ጥሎ ማለፍ ውድድር ተሳታፊ የነበረው አርባምንጭ ከተማ በውጤት ማጣትና በደካማ አቋም ላይ መገኘቱን ተከትሎ የአርባ ምንጭ እግር ኳስ ክለብ ቦርድ በዛሬው ዕለት አስቸኳይ ስብሰባ አድርጓል።

በክለቡ የበላይ ጠባቂ እና በክለቡ የቦርድ ሰብሳቢ በእጩነት ከቀረቡና በጊዜያዊነት እንዲያገለግሉ የታጩ የአሰልጣኝ ቡድንን ጨምሮ ሌሎችን የቦርድ አባላትን ተቀብሎ በመወያዬት በሙሉ ድምፀ አፅድቋል።

በፀደቀው ውሳኔ መሰረት ፦

1.አበባው ቡጣቆ የክለቡ ጊዜያዊ አሰልጣኝ
2.ታረቀኝ አርጌቦ የክለቡ ምክትል ጊዜያዊ አሰልጣኝ
3.ሰለሺ ሺፈራው የክለቡ ጊዜያዊ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ሆነው እንዲያገለግሉ በመሉ ድምፅ ውሳኔ አፅድቋል።

የክለቡ እጣፈንታን በበላይነት የሚመራው የአስተዳደር ቦርድ ከዚህ በፊት ከነበረው በእጅጉ የተሻለና የተቀናጀ አሰራር በመዘርጋት በሙል ጊዜ ከፍተኛ ክትትልና ድጋፍ የሚሰጥ አመራር መመደብ እንደሚገባ በመግለፅም፥

1.አቶ ትግሉ ኃይሌ የክለቡ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ

  1. አቶ አየናቸው ውበቴ
    3.የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ
    4.የአርባምንጭ ትምህርት ኮሌጅ
    5.የአርባምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
    6.የጋሞ ልማት ማህበር
    7.የጋሞ ዞን እና የአርባምንጭ ከተማ ፋይናንስና ፕላን መምሪያ
    8.የጋሞ ዞን እና የአርባምንጭ ከተማ ባህልና ስፖርት መምሪያን ጨምሮ ለክለቡ በእጅጉ የሚሰሩና የሚተጉ አካላት ያካተተ በጥቅሉ 15 አባላት ያለው ቦርድ እንዲቋቋም ውሳኔ አስተላልፏል።

የክለቡን ቀጣይ ጨዋታዎች ሙያዊ ዕውቀት ባለው ጊዜያዊ ቴክኒክ ቡድን እንዲመሩ፦

  1. ዶ/ር ኤፍሬም ከንቲባ
    2.አቶ አሰግድ ከተማ
    3.አቶ ቸኮል ታዬን በመምረጥ በሙሉ ድምፅ ውሳኔውን አፅድቋል።

በተጨማሪም በቅርቡ ወደ ክለቡ የተቀላቀሉት አቶ ፀጋዬ ጊሌ የቡድኑ መሪ እና አቶ ፍላጎት ኤልዶ የክለቡ ቴክኒካል ዳይሬክተር ሆነው በነበሩበት እንዲቀጥሉና ከቦርድ አባላት አቶ ማሞ ደቦጭና አቶ በስልጣኑ ጌታቸው ባላቸው የክለቡ ኃላፊነት በጋራ እንዲሰሩ ሲውሳኔውን አሳውቋል።

በመድረኩ የአርባ ምንጭ ከተማ ከንቲባና የክለቡ ቦርድ ሰብሳቢ መስፍን መንዛ (ዶ/ር)፣የክለቡ የበላይ ጠበቂና የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ደምስ አድማሱ፣ አቶ ትግሉ ኃይሌ የክለቡ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ጨምሮ የደጋፊ ማህበር አባላትና የከተማው አመራሮች ታድመዋል።