አርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ አዲሴ ካሳን ዋና አሰልጣኝ በማድረግ ሾሟል!

የአርባ ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ቦርድ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ በውጤት ማጣትና በፕሪምየር ሊጉ ላይ ደካማ የውድድር ጉዞ በማድረጉ ከቀደመው አሰልጣኝ በረከት ደሙ ጋር በመለያየት በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ያለፉ የስምንት ሳምንታት ጨዋታዎችን በቀድመው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጫወት ያሳለፈውን አበባው ቡጣቆን ምክትል አሰልጣኝነት ቡድኑን እየመራ መቆየቱ ይታወሳል ።

ሆኖም ክለቡ የተፈለገውን ውጤት ባለማምጣቱ ምክንያት በቦታው ልምድ ያለውን ቋሚ ዋና አሰልጣኝ መቅጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የክለቡ ቦርድ አሰልጣኝ አዲሴ ካሳ ክለቡን በዋና አሰልጣኝ ሆኖ እንዲመራ መወሰናቸውን ገልፀዋል ።

ክለቡ ካለበት ዝቅተኛ ደረጃና የውጤት ማጣት በማውጣት ወደተሻለ ውጤት እንዲያደርስ ከቦርዱ ኃላፊነት ውሰደው በይፋ የተሰየሙት ዋና አሰልጣኝ አዲሴ ካሳ ከዚህ ቀደም በሀዋሳ ከተማ ም/አሰልጣኝ እንድሁም በዋናነት ፣ በደቡብ ፖሊስ ፣ ወልቂጤ ከተማ ፣ ካፋ ቡና ፣ ቡታጅራ ከተማ በቅርብ ዓመታት ሲዳማ ቡናን ምክትል እና በዋና አሰልጣኝነት መምራት የቻሉ አሰልጣኝ ናቸው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *