ባካሪ ሳኛ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በመገኘት ውይይት አድርጓል።

የቀድሞው የአርሰናል፣ ማንቸስተር ሲቲ እና ፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ባካሪ ሳኛ በትናንትናው እለት ወደ አዲስ አበባ መምጣቱ የሚታወቅ ሲሆን በዛሬው ዕለት በፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት ተገኝቶ ልምዱን አካፍሏል።

ሳኛ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁን ጋር ባደረገው ውይይት ፌዴሬሽኑ በወጣቶች እግር ኳስ ልማት ላይ ሊሰራቸው ስለሚገቡ ሥራዎች እና ልንከተለው በሚባው ተሰጥኦን በለጋ እድሜ የመለየት ሂደት ዙርያ ያተኮረ ሲሆን ሳኛ ባቋቋመው የወጣቶች እግር ኳስ ልማት ተቋም ተሰጥኦ ልየታ (talent identification) በምን መልኩ እንደሚከናወን ገለጻ አድርጓል። በእግር ኳስ ህይወቱ ካሳለፈው ልምድ በመነሳትም ወጣቶች ሊቀስሙ ስለሚገባቸው ጉዳዮች ልምዱን አጋርቷል።

ባካሪ ሳኛ በቆይታው ማብቂያ ባሕላዊ ልብስ እና የፌዴሬሽኑ ብራንድ የሆነው ሀገሬ ኳስ በማስታወሻነት ተበርክቶለታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *