በአዳማ ከተማ ለሶስት ወራት ለመጠጋ ጊዜ ሲካሄድ በነበረው የመጀመሪያው ዙር የኢትዮጵያ ሊግ አንድ ልደታ ክ/ከተማ አስተዳደርን ወክሎ ሲሳተፍ የነበረው የልደታ ክፍለ ከተማ የወንዶች እግርኳስ ከለብ አንደኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀ
ምንም ዓይነት ሽንፈት ያላስተናገደው ልደታ ክፍለ ከተማ የወንዶች እግርኳስ ቡድን በአጠቃላይ ካደረጋቸው 16 ጨዋታዎች ውስጥ 10 ጨዋታዎችን በማሸነፍና 6 ጨዋታዎችን አቻ በመለያየት 36 ነጥቦችን በመሰብሰብ የመጀመሪያ ዙር የኢትዮጵያ ሊግ አንድ ምድብ ሀ አንደኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቅ ችሏል።
ይህ ውጤት እንድመዘገብ የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ድጋፍ እንደተደረገላቸው አሰልጣኞች፣ ተጫዋቾችና የክለቡ አመራሮች ተናግረዋል።
በቀጣይ ለሚደረገው 2ኛ ዙር ውድድር ከዚህ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብና ወደ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ለማደግ ጠንክረው እንደሚሰሩ ያስታወቁት የአሰልጣኝ ቡድን አባላት እንድሁም ተጨዋቾች በቀጣይም የክፍለ ከተማው አስተዳደር ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አስተላልፈዋል።
