በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት በሚካሄደው የ2018 አዲስ አበባ ሊግ የሚሳተፈው አብዲ ቦሩ እግር ኳስ ክለብ አዳዲስ ተጨዋቾችን አስፈርሟል።
በዋና አሰልጣኝ አበበ ተስፋዬ የሚመራው አብዲ ቦሩ እግር ኳስ ክለብ ለውድድሩ ቅድመ ዝግጅቱን በፉሪ ሜዳ እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን ኦሳማ ረድዋን ፣ ኡካን ቶማስ ፣ ዋድ ባም ፣ ሉል ቾል ፣ ቻንኮል ጆን ፣ ከድር መሀባ ፣ አብነት አባር ፣ መሐመድ ሸምሱ ፣ ሐብታሙ ብርሃኑ እና ያበፅ ሙላቱን ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል።




















