በኦሮሚያ ፕሪሚየር ሊግ የሚሳተፈው ሰበታ ክፍለ ከተማ በኢትዮጵያ ሊግ አንድ በርካታ አመታትን በወሊሶ ከተማ አሰልጣኝነት የሚታወቀውን ዳንኤል ጌታቸውን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል ።
ዛሬ በሰበታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በተደረገው የፊርማ ስነ-ስርዓት የሰበታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ደበላ ጫካ እንደተናገረው ዘንድሮ ሰበታን ወደ ቀድሞ ከፍታው ለመመለስ ጽ/ቤቱ ከአሰልጣኙ እንድሁም ከክለቡ ጎን መሆኑን ተናግሯል።
