በሱሉልታ ከተማ ታዳጊዎችን በማሰልጠን ከ15 ዓመት በታች እና ከ17 ዓመት በታች የጀመረው የአሰልጣኝነት ህይወት ኦሮሚያ ሊግ በ2000 ዓ.ም እስከ 2002 ዓ.ም ከአሰልጣኝ በኋይሉ ጋር ለሱሉልታ ከተማ ለክለቡ እየተጫወተ እንድሁም ም/አሰልጣኝ በመሆን የኦሮሚያ አሸናፊዎች አሸናፊ ፣ መላው የኦሮሚያ ሻምፕዮና ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን ውድድር እና የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፕዮና ዋንጫ በማንሳት ቡድኑን ወደ ኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ (ብሔራዊ ሊግ) በማሳደግ በአንድ ዓመት አራት ዋንጫ ማሳካት ችሏል።
ከሱሉልታ ከተማ ጋር 2003 ዓ.ም በም/አሰልጣኝነት እንድሁም በተጨዋችነት ወቅት ባጋጠመው ጉዳት ከውድድሩ አጋማሽ አከባቢ ጀምሮ ኳስ መጫወት በመተው ሙሉ በሙሉ ወደ አሰልጣኝነት ፊቱን በማዞር በምክትል አሰልጣኝ መስራት የቻለ።
2004 ዓ.ም እስከ 2005 ዓ.ም በም/አሰልጣኝ ከጳውሎስ ጌታቸው (ማንጎ ) ጋር ከሰራ በኋላ 2006 በምክትል አሰልጣኝነት ከታደሰ ጥላሁን ጋር የአንደኛ ሊግ ምድብ ዋንጫ ማንሳት የቻለ ሲሆን ባህር ዳር ላይ በተካሄደው የማጠቃለያ ውድድር ላይ ፕሪሚየር ሊግ ለማደግ ጫፍ ደርሶ አዳማ ባደገበት ዓመት ሱሉልታ 3ኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቅ ችሏል።
2007 ዓ.ም እስከ 2010 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሊግ ም/አሰልጣኝ በመሆን ከታደሰ ጥላሁን ጋር የምድብ ዋንጫ በማንሳት በዛ ዓመት በተካሄደው የማጠቃለያ ውድድር (የቶርናመንት )ዋንጫ በማንሳት ድሬዳዋ ላይ በተደረገው ውድድር ወደ ከፍተኛ ሊግ ማሳደግ የቻለ ሲሆን ክለቡ ወደ ከፍተኛ ሊግ ካደገ በኋላ ከ2008 እስከ 2010 በከፍተኛ ሊግ ከታደሰ ጥላሁን ጋር መስራት ችሏል።
2011 ዓ.ም እና 2012 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሊግ አንድ ዋና አሰልጣኝ በሱሉልታ ከተማ

2013 ዓ.ም በሱሉልታ ምክትል በኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ አሰልጣኝ ከሰራ በኋላ 2014 ዓ.ም በአንደኛ ሊግ ሊግ ዋና አሰልጣኝ በምድብ ጨዋታ 3ኛ ደረጃ ይዞ በማጠናቀቅ ድሬዳዋ ላይ በተካሄደው የማጠቃለያ ውድድር መሳተፍ የቻለ
2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የምድቡን ዋንጫ እንድሁም በማጠቃለያ ውድድር ዋንጫ በማንሳት ወደ ከፍተኛ ሊግ ማሳደግ የቻለ አሰልጣኝ ሲሆን በሸገር ከተማ ምስረታ ጋር ተያይዞ ክለቡ መቀጠል ሳይችል ቀርቷል።
2016 ዓ.ም/አሰልጣኝ በሸገር ከተማ ከጥላሁን ተሾመ ጋር መስራት የቻለ
2017 ዓ.ም ከሱሉልታ ክፍለ ከተማ ጋር ጥሩ የውድድር ጊዜ በማሳለፍ የቻለው አሰልጣኝ ሰለሞን አዳነ በ2018 ከቡድኑ ጋር ለመቀጠል ከስምምነት ላይ ደርሷል።


አሰልጣኝ #ሰለሞን እግር ኳስ ዉስጥ እሰከ ዘሬ ድረስ ያለፉበትን እና የአሳለፈዉን ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻ አንብቤያለሁ። እዉነትም ነዉ።
እህ የሚያሳየን በስፖርት ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጥሩ መሆን ከባድ አይደለም። ከባድ የሚሆነው በየቀኑ ጥሩ መሆን ነው። እህ አሰልጣኝ እህዢች አገር ዉስጥ ጥሩ ልምድና የለፈበት ዉጠዉረዶችም ማካፈል የምችል ነዉና #በርታ እንድሁ ቀጥል እኒላሌን። መልካም የስራ ዘመን ለማለት እንወዳለን።