መቐለ 70 እንደርታ ሶስት ጨዋታዎች በፊርፌ ተሸናፊ እንድሁን ቅጣት ተላለፈ!
መቐለ 70 እንደርታ እግር ኳስ ክለብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በነበረው 7ኛ ሳምንት ጨዋታ በ 2017 ውድድር ዘመን 30ኛ (የመጨረሻው ሳምንት) ጨዋታ በቀይ ካርድ ከሜዳ የተወገደውንና አራት ጨዋታ እንድታገድ የተወሰነበትን ሱለይማን ሃሚድ መታወቂያ ቁጥር EFF-18-77/ የተባለ ተጫዋች ያለፉትን 6 ጨዋታዎች አሰልፎ ስለማጫወቱና በዚህም የፎርፌ ውጤት ይገባኛል በማለት ከኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ክስ ቀርቦበታል።
የውድድር ስነ-ስረዓት ኮሚቴ የቀረበውን ክስ መነሻ በማድረግ ባካሄደው ማጣራት ተጨዋቹ ለመቐለ 70 እንደርታ በ2ኛ ሳምንት ከመቻል ፣ በ3ኛ ሳምንት ድሬዳዋ ከተማ እና በ4ኛ ሳምንት ከሀዋሳ ከተማ በተደረጉ ጨዋታዎች ቅጣቱን ሳይጨርስ ተሰልፎ እንዳጫወተ አረጋግጧል።
ስለሆነም ክለቡ /መቐለ 70 እንደርታ/ ተገቢ ያልሆነ ተጨዋች አሰልፎ በማጫወቱ ለፈፀመው ጥፋት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 5 አንቀጽ 36 (ሐ) መሰረት ከ2ኛ እስከ 4ኛ ሳምንት ያሉትን 3 ጨዋታዎች ውጤት ተሰርዞ በፎርፌ ተሸናፊ እንዲሆን (ሶስቱንም ጨዋታዎች 0 ነጥብ እና 3 የግብ እዳ እንድመዘገብበትና እና ለተጋጣሚዎቹ መቻል ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ 3 ነጥብና 3 ነጥብ እንድመዘገብላቸው/ በተጨማሪም ብር 20ሺህ/ እንድከፍል እንዲሁም የቡድን መሪው 6 ወር እንድታገድ የውድድር ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
