መቐለ 70 እንደርታ ሁለት የውጭ ዜጋ ተጨዋቾችን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል !

ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሀያ አራት አድርጎ 23 ነጥቦችን በመሰብሰብ 19ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው መቐለ 70 እንደርታ ሁለት የውጭ ዜጋ ተጨዋቾችን አስፈርሟል።

የመጀመሪያው ተጨዋች ናይጄሪያዊው አጥቂ አይባሚ ፕሪንስ ኦፊሬ ሲሆን ከዝህ ቀደም አጥቂው ለእስራኤሉ ማካቢ አታ ቢያሊክ እና የቆጵሮስ ፕሪምየር ሊግ ክለብ አክሪታስ ክሎራካሲ የተጫወተ ሲሆን መቐለ 70 እንደርታን ተቀላቅሏል።

ሌላኛው መቐለ 70 እንደርታን የተቀላቀለው ኮት ዲቯራዊው የ23 ዓመቱ አማካይ ስፍራ ተጨዋች አብዱለጢፍ ባምባ ሲሆን ከዚህ ቀደም ሳንፔድሮ ፣ ሬሲንግ ክለብ አቢጃን ፣ ኤሴክስ ሜሞሴስ ፣ ለአንጎላው ሳግራዳ ፣ አል ሱልፍም ፣ ለደቡብ አፍሪካው ቲ.ኤስ ጋላክሲ ፣ በጋናው አድዋና ስታርስ እና ስታደ አቢጃን የተጫወተው አብዱላጢፍ ባምባ ምዓም አናብስትን የተቀላቀለ ተጨዋች ሆኗል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *