መሳይ ተፈሪ በድጋሚ ወላይታ ድቻን ለማሰልጠን ከስምምነት ላይ ደርሷል!

በውጤት ቀውስ ምክንያት ዋና አሰልጣኝ የነበረውን ገ/ክርስቶስ ቢራራን ያሰናበተው ወላይታ ድቻ የቀድሞ አሰልጣኙን በድጋሚ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ለመሾም ከስምምነት ላይ ደርሷል።

የጦና ንቦቹ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ያሳደጋው የቀድሞ አሰልጣኙ መሳይ ተፈሪ ወደ ቀድሞ ቤቱ ተመልሶ ለመሥራት ከስምምነት ላይ ደርሷል።

መሳይ ተፈሪ ከወላይታ ድቻ በተጨማሪ አርባ ምንጭ ከተማን ወደ ፕሪሚየር ሊግ ማሳደግ የቻለ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በም/አሰልጣኝ እንድሁም ዋና አሰልጣኝ በመሆን እያሰለጠነ የሚገኝ አሰልጣኝ ነው።