የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ከጊኒ ቢሳው እና ቡርኪና ፋሶ ጋር ለሚያደርጋቸው የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዎች ዝግጅት አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ለ20 ተጫዋች ጥሪ አድርገዋል።

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች እሁድ መስከረም 18 እስከ 8:00 በጁፒተር ሆቴል ተገኝተው ሪፖርት በማድረግ ዝግጅት እንዲጀምሩ ጥሪ ቀርቧል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጊኒ ቢሳውን በሩዋንዳው አማሆሮ ስታዲየም መስከረም 28 ሲያስተናግድ ከቡርኪናፋሶ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ዋጋዱጉ ላይ ጥቅምት 2 ይከናወናል።