ኮንሶ ኒዮርክ ዘጠኝ አዳዲስ ተጨዋቾችን አስፈርሟል!

በኢትዮጵያ ሊግ አንድ ምድብ ሀ በዘንድሮ የውድድር ዓመት 19 ጨዋታዎችን አድርጎ 26 ነጥቦችን በመሰብሰብ 9ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ኮንሶ ኒውዮርክ እግር ኳስ ክለብ ሁለተኛ ዙር ጠንካራ ተሳታፊ ሆኖ ለመቅረብ ዘጠኝ ተጨዋቾችን በዛሬው ዕለት አስፈርሟል።

በ2017 ጂንካ ከተማ ላይ በተካሄደው ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፕዮና ውድድር ላይ ኮንሶ ኒውዮርክ ሻምፕዮን ሲሆን የቡድኑ ግብ ጠባዊ የነበረው እንድሁም የውድድሩ ኮከብ ግብ ጠባቂ ሽልማት ያሸነፈው ተመስገን እስራኤል ግማሽ የውድድር ዓመት በፉሪ ክ/ከተማ ቆይታ ካደረገ በኋላ በድጋሚ ወደ ኮንሶ ኒውዮርክ ተመልሶ ፊርማውን አኑሯል።

ከዝህ ቀደም በሠመራ ዩንቨርሲቲ ተጫውቶ ያሳለፈው እና በ2018 የአዲስ አበባ ሊግ የአብዲ ቦሩ እግር ኳስ ክለብ አጥቂ ስፍራውን ሲመራ የነበረው ሕዝቅኤል ተስፋዬ ኮንሶ ኒውዮርክን ተቀላቅሏል።

በአርባ ምንጭ ከተማ ተስፋ ቡድን የጀመረው የእግር ኳስ ህይወቱ ወደ ዋናው ቡድን ካደገ በኋላ ወሎ ኮምቦልቻ ፣ ጎፋ ባራንቼ እና ጉለሌ ክ/ከተማ ከተማ ተጫውቶ ያሳለፈው አማካይ ስፍራ ተጨዋች ኮንሶ ኒውዮርክ ተቀላቅሏል።

ከዝህ ቀደም ጋሞ ጨንቻ ቆይታ የነበረው አማካይ ስፍራ ተጨዋቹ ምንተስኖት መስፍን በአዲስ አበባ ሊግ አብዲ ቦሩ እግር ኳስ ክለብ ከተጫወተ በኋላ ለኮንሶ ኒውዮርክ ፊርማውን አኑሯል።

በ2017 ጂንካ ከተማ ላይ በተካሄደው ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፕዮና ውድድር ላይ ኮንሶ ኒውዮርክ ሻምፕዮን ሲሆን የቡድኑ የግራ መስመር ተከላይ ስፍራ ተጨዋች የነበረው ታምራ ዮሴፍ ግማሽ የውድድር ዓመት በፉሪ ክ/ከተማ ቆይታ ካደረገ በኋላ በድጋሚ ወደ ኮንሶ ኒውዮርክ ተመልሶ ፊርማውን አኑሯል።

ከዝህ ቀደም ጂንካ ፣ ሐረር ከተማ እና ሆለታ ከተማ መጫወት የቻለው አሸናፊ ኋይለማርያም ኮንሶ ኒውዮርክን ተቀላቅሏል።

ከዝህ ቀደም ይርጋጨፌ ቡና ጉለሌ ክፍለ ከተማ እና ባቱ ከተማ ተጫውቶ ያሳለፈው ውብሸት ኋይሌ ኮንሶ ኒውዮርክን ተቀላቅሏል።

ከዝህ ቀደም በጂንካ ከተማ ተጫውቶ ካሳለፈ በኋላ በ2017 ጂንካ ከተማ ላይ በተካሄደው ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፕዮና ውድድር ላይ ኛንግላንድ 3ኛ ደረጃ ይዞ ሲያጠናቅቅ የቡድኑ የፊት መስመር ስፍራ ተጨዋች የነበረው ናኩታ ምትኩ ግማሽ የውድድር ዓመት በኛንግላንድ ቆይታ ለ ኮንሶ ኒውዮርክ ፊርማውን አኑሯል።

ሌላኛው አብዱራሒማን ቡሳሪ  ከሰበታ ክፍለ ከተማ ኮንሶ ኒውዮርን የተቀላቀለ ተጨዋች ሆኗል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *