አንተነህ ተፈራ የጣና ሞገዶቹን ተቀላቀለ!

ከዝህ ቀደም በኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፕዮና ከሻኪሶ ከተማ የተገኘው ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ቡና ጥሩ ቆይታ ካደረጉ አጥቂዎች አንዱ የሆነው አንተነህ ተፈራ ዘንድሮ አዲስ አዳጊውን ሸገር ከተማን ተቀላቅሎ የነበረ ቢሆንም በስምምነት ክለቡን በመልቀቅ ወደ ባህር ዳር ከተማ አቅንቷል።

በ 2017 ለኢትዮጵያ ቡና 10 ግቦችን በማስቆጠር በዚህ ውድድር ዓመት ሸገር ሲቲን የተቀላቀለው ተጨዋቹ በግማሽ የውድድር ዓመት ባደረጋቸው ጨዋታዎች ሁለት ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል ።

አንተነህ ተፈራ በባህር ዳር ከተማ አንድ ዓመት ከስድስት ወር የሚያቆነውን ፊርማ ከደቂቃዎች በፊት በፌደሬሽን ተገኝቶ መፈረሙን ክለቡ አስታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *